ብርሃን ለሃገር ሁሉ

ውድ የሀገራችን ቤተሰቦች በመተሐራ በተጠናከረና በተደራጀ መልክ የቤተሰብ አብሮነት ማሳያ በሚሆን ድጋፍ ስራዎቻችንን ጀምረናል በዚህም "ብርሃን ለሃገር ሁሉ " / " Berhane Lehager Hulu " በሚል አንድ አመት ለሚጠጋ ጊዜ ሲሰራበት የነበረውን የአሰራር ስርአት ወይም መዋቅር በማደራጀት በወር ሁለት ጊዜ ከመላው አባላቱ ጋር በመወያየት አላማውን አንድ ነገር ላይ ብቻ ትኩረት አድርጎ በመስራት በዋናነት እገዛ ከሚፈልጉ ቤተሰቦቻችን ጋር አብረናቸው በመሆን ለታናናሽ ወንድም እህቶቻችን ለትምህርታቸው የሚስያፈልገውን ማንኛውም ነገር በማገዝ ለ 2015 ዓ/ም በ 20 ተማሪዎች አሀዱ ብለን ጀምረናል ። ከዋና ዓላማችን ውጪ ያሉ የተለያዩ ችግሮች ቤተሰቦቻችን ጋር እንዳሉ ብንረዳም በዚህ ወቅት ከትምህርት ድጋፍ ውጪ #ፈፅሞ የተለየ ዓላማ ይዞ መንቀሳቀስ የማይቻል በመሆኑ ከመተዳደሪያ ደንብና ከውስጥ አሰራሮች ውጪም ግለኝነትን ማንፀባረቅም #ክሬዲት ለመውሰድ መሞከርም እንደ ቤተሰብ የመተሐራን ቤተሰብ ስለማይመጥን ከአስተባባሪዎች ጀምሮ ማንኛውም የማህበሩ አባል በዚህ ጉዳይ እንዳይሳተፍ የተወሰነ ስለሆነና ይህንንም የሚያከብር ሲሆን ይህንን ተላልፎ የሚገኝ የማህበሩ አባል ካለም እስከ ከማህበሩ አባልነት #መሰናበት ሊወሰን ይችላል ። ማህበሩ ስራውን ከጀመረ አንስቶ እስከ አምስት አመት ባለው ጊዜ የማህበሩ ቤተሰባዊነት ተጠብቆ በአካባቢያችን ባሉ ትምህርት ቤቶች እስከ አንድ ሺ /1,000 / የሚደርሱ ተማሪዎችን ለትምህርት በሚያስፈልጉ ቁሳቁስ :- ቦርሳ ፣ ደብተር ፣ ዩኒፎርም ፣ አጋዥ መፅሀፍት ፣ እስኪብርቶ ፣ እርሳስ ፣ ላጲስ ፣ ኮምፓስ ፣ እንዲሁም አመታዊ አስጠኚ ፣ የስነልቦና እና ሌሎች እገዛዎችንም ለማድረግ በዋናነት የማህበሩ ራዕይ አድርጐ አስቀምጧል ። በቀጣይም ከሀገር አቀፍ ተቋማት ፣ አለም አቀፍ NGOዎች ፣ ከመንግስት ተቋማትና ሌሎችም ጋር ለመስራት ተስማምተን ጨርሰናል።

ከምንሰራቸው ስራዎች ጅማሮውን በአዲስ ከተማ / ሀሮ አዲ / ጡረታ ሰፈር አድርገን ጀምረናል። ቤተሰቦቻችንን በተመለከተ እጅግ ሚስጥራዊ በሆነ ጥብቅ የመረጃ አያያዝ በመከተል ክትትል የምናደርግ ሲሆን ማህበራችንም በተለያዩ ዘርፎች አስተባባሪዎችና የአመራር አባላት የተዋቀረ ስለሆነ ማህበሩን በመወከል ከማህበሩ አስተባባሪዎች የጋራ እውቅና ውጪ የትኛውም ግለሰብም ሆነ ቡድን የከረዩ ማህበርን እንደማይወክል ተረድታችሁ በህግና በምንመራበት አሰራር ማህበራችንን መቀላቀል የሚቻል ሲሆን የማህበሩም ተጠሪ አድርገን የወከልነው አርአያ መካሻን በስልክ ቁጥር 0919151212 ደውለው በቀጥታ በማግኘት መረጃ መቀበል የሚችሉ መሆኑና በተጨማሪ ከማህበሩ የፌስ ቡክ ገፅ፣የቴሌግራም ግሩፕ እንዲሁም የዩቲዩብ ቻናል ውጪ ኮፒ ፔስት ተደርገው ኤዲት ተደርጎ የሚለቀቁ መረጃዎች በሙሉ ማህበራችንን የማይወክልና ቤተሰባዊ እገዛን ሊረብሹ የሚችሉ አካሄዶች መሆኑን ተረድታችሁ በፍፁም ቅንነትና ቤተሰባዊነት መረጃዎቻችንን #ሼር በማድረግ ለሀገር ተወላጆችና ለወዳጆቻችሁ እንድታሳውቁልን በአክብሮት እየጠየቅን በተለያዩ አጋጣሚዎች መረጃዎቹን ሰምታችሁ ማገዝ የምትፈልጉ በወር 100 ብር በመለገስ ለቤተሰቦቻችን ለመቆም ከወሰናችሁ ከስር በተቀመጡት የማህበራዊ ሚዲያ አድራሻዎቻችን ሊያገኙን ይችላሉ ።

ይህንን የቤተሰብ ድጋፍ በማገዝ ዘመናትን የሚሻገር መልካም አሻራችንን በጋራ እናሳርፍ ።

ለበለጠ መረጃ በስ/ቁ

0912151212 አርአያ መካሻ

0921254646 ላምሮት አየለ

0945827649 ሰብለ ስንታየሁ

በአጠቃላይ በማህበራዊ ሚዲያ እንዲከታተሉን ከስር ባሉት ሊንኮች መረጃዎችን እናጋራለን ላይክ ሰብስክራይብ እና ሼር ያድርጓቸው

ቴሌግራም https://t.me/+f12JiUaJ2-E0Mjk0
ዩቱዩብ https://www.youtube.com/channel/UCkKYp1ZiuEgkxkbvihPl_RA